• Call Us
  • +25146 554 16 87

የእርሻ ልማት ዘርፍ

የሚሰጡ አገልግሎቶች፦

በቢሮ ም/ሀላፊ የሚመራ የእርሻ ልማት ዘርፍ ተጠሪነቱ ለግብርና ቢሮ ሀላፊ ሆኖ የሚከተለውን ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል፡-

የእርሻ ልማት ዘርፍ ምርታማነት ለማሻሻል ለአርሶ አደሩ፣ ለግል ባለሀብቱና በሰብል ልማት ለተሰማሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጡ የኤክስቴንሽንና የስልጠና አገልግሎት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤

የአየር ንብረት ለውጥ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ተመጋጋቢነት እንዲጎለብት ሥርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊነቱን ይከታታላል፣ ይመራል፤

ስነ-ምህዳርና ከባቢ አየርን መሠረት ያደረጉ የግብርና አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎችን በሰብል አመራረት ስርዓቱ ውሰጥ ውጤታማነትና ዘላቂ ልማት በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲተገበሩ ያደርጋል፣ በዘርፋ የሚሰሩ አካላትንም ይደግፋል፣

የመነሻ ዘር ብዜትን ያስተባብራል፣ ስርዓቶችን ያዘጋጃል ተግባራዊ ያደርጋል፣ እንዲሁም የዘር ብዜት ሥራ የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያገኝ ያደርጋል፣

የአየር ንብረት መረጃን መሠረት ያደረገ የሰብል ልማት ምክረ ሀሳብ በዘመናዊና ተደራሽ በሆነ መልኩ ለአርሶ አደሩ እንዲደርስ ያደርጋል፤

የምርት ብክነትን ለመቀነስ እና የምርት ጥራትን ለማሻሻል የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችና አሰራሮችን ይለያል፣ የምርምር ስራዎች እንዲሰሩ ይደግፋል፣ ለአርሶ አደሩና ለግል ባለሀብቱ እንዲደርሱ ያደርጋል፣ ውጤታማነታቸውን ይገመግማል፤

የመደበኛ ተባዮች ጉዳትን ለመቀነስ የሚረዱ ከዘር ጀምሮ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ ከባቢ አየርን በማይጎዳ መልኩ ተደራሽ ያደርጋል፤

ዘርፍን ለማዘመን የሚረዱ ዕውቀትና ክህሎትን ለማሻሻል የሚያግዙ ስልጠናዎች ይለያል፣ የአጭርና የረጅም ጊዜ አቅም ግንባታዎች እንዲሰጡ ያደርጋል፣ ይመራል፤

ለዘርፉ ልማት ምርታማነትና ዕድገት ዘለቄታዊ ልማት አጋዥ የሆኑ ስትራቴጂዎችንና አቅጣጫዎችን በማሳየትና በማዘጋጀት የሀብት ምደባ በማመቻቸት የቁጥጥርና ክትትል ድጋፎችን በማድረግ የግብርናን ይመራል፤

ለዕቅድና ለውሳኔ አሰጣጥ ድርሻ ያላቸውን የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት መረጃዎች ከባለደርሻ አካላት ጋር በመሆን ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል፤

የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ግቦችን ሊያሳኩ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን፣ፓኬጆችንና አሰራሮችን ይለያል፣ ይመርጣል፣ ቴክኖሎጂዎችና የመፍትሄ ሀሳቦች በኤክስቴንሽን ስርዓቱ እንዲስፋፉ ይመራል፣ ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል፤

ዘርፉ ከስሩ የሚከተሉት ዳይሬክቶሬቶች ያስተባብራል፡-

            o የሰብል ልማት ዳይሬክቶሬት

            o የሆርቲካልቸር ልማት ዳይሬክቶሬት

            o የእርሻና ሆርቲካልቸር ኤክስቴንሽን ዳይሬክቶሬት