CERS-Bureau of Agriculture
በቢሮ ም/ሀላፊ የሚመራ የእርሻ ልማት ዘርፍ ተጠሪነቱ ለግብርና ቢሮ ሀላፊ ሆኖ የሚከተለውን ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል፡-
O የእርሻ ልማት ዘርፍ ምርታማነት ለማሻሻል ለአርሶ አደሩ፣ ለግል ባለሀብቱና በሰብል ልማት ለተሰማሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጡ የኤክስቴንሽንና የስልጠና አገልግሎት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
O የአየር ንብረት ለውጥ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ተመጋጋቢነት እንዲጎለብት ሥርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊነቱን ይከታታላል፣ ይመራል፤
O ስነ-ምህዳርና ከባቢ አየርን መሠረት ያደረጉ የግብርና አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎችን በሰብል አመራረት ስርዓቱ ውሰጥ ውጤታማነትና ዘላቂ ልማት በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲተገበሩ ያደርጋል፣ በዘርፋ የሚሰሩ አካላትንም ይደግፋል፣
O የመነሻ ዘር ብዜትን ያስተባብራል፣ ስርዓቶችን ያዘጋጃል ተግባራዊ ያደርጋል፣ እንዲሁም የዘር ብዜት ሥራ የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያገኝ ያደርጋል፣
O የአየር ንብረት መረጃን መሠረት ያደረገ የሰብል ልማት ምክረ ሀሳብ በዘመናዊና ተደራሽ በሆነ መልኩ ለአርሶ አደሩ እንዲደርስ ያደርጋል፤
O የምርት ብክነትን ለመቀነስ እና የምርት ጥራትን ለማሻሻል የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችና አሰራሮችን ይለያል፣ የምርምር ስራዎች እንዲሰሩ ይደግፋል፣ ለአርሶ አደሩና ለግል ባለሀብቱ እንዲደርሱ ያደርጋል፣ ውጤታማነታቸውን ይገመግማል፤
O የመደበኛ ተባዮች ጉዳትን ለመቀነስ የሚረዱ ከዘር ጀምሮ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ ከባቢ አየርን በማይጎዳ መልኩ ተደራሽ ያደርጋል፤
O ዘርፍን ለማዘመን የሚረዱ ዕውቀትና ክህሎትን ለማሻሻል የሚያግዙ ስልጠናዎች ይለያል፣ የአጭርና የረጅም ጊዜ አቅም ግንባታዎች እንዲሰጡ ያደርጋል፣ ይመራል፤
O ለዘርፉ ልማት ምርታማነትና ዕድገት ዘለቄታዊ ልማት አጋዥ የሆኑ ስትራቴጂዎችንና አቅጣጫዎችን በማሳየትና በማዘጋጀት የሀብት ምደባ በማመቻቸት የቁጥጥርና ክትትል ድጋፎችን በማድረግ የግብርናን ይመራል፤
O ለዕቅድና ለውሳኔ አሰጣጥ ድርሻ ያላቸውን የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት መረጃዎች ከባለደርሻ አካላት ጋር በመሆን ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
O የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ግቦችን ሊያሳኩ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን፣ፓኬጆችንና አሰራሮችን ይለያል፣ ይመርጣል፣ ቴክኖሎጂዎችና የመፍትሄ ሀሳቦች በኤክስቴንሽን ስርዓቱ እንዲስፋፉ ይመራል፣ ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
O ዘርፉ ከስሩ የሚከተሉት ዳይሬክቶሬቶች ያስተባብራል፡-
o. የሰብል ልማት ዳይሬክቶሬት
o. የሆርቲካልቸር ልማት ዳይሬክቶሬት
o. የእርሻና ሆርቲካልቸር ኤክስቴንሽን ዳይሬክቶሬት
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU