CERS-Bureau of Agriculture
የ5 በ5 የከተማ ግብርና ፕሮጀክት (5 የአትክልት አይነት በቤተሰብ)፡
ይህ ፕሮጀክት ‘’ምግቤን ከጓሮዬ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ነው። ይህ ፕሮጀክት በከተማ የሚኖር ሁሉም ነዋሪ ቪላ ይሁን ፎቅ ላይ የሚኖር እያንዳንዱ ነዋሪ ቢያንስ 5 የአትክልት አይነት ይኖረዋል። ከእያንዳንዱ አትክልት 5 (አምስት) ፍሬ ያለማል ማለት ነው። በዚህ መሰረት በአንድ ቤተሰብ ግቢ ወይም መኖሪያ አካባቢ በትንሹ ሀያ አምስት አትክልቶችን ያለማል ማለት ነው። ይህ ኢኒሺዬቲቭ “ግብርና የገጠር ስራ ነው” የሚለው የተለመደዉ አስተሳሰብ መቀየር ያስቻለም ስልት ነው፡፡ በአሁኑ ዓመትም አዳዲስ የከተማ ግብርና ሥፍራዎችን የተጀመሩ ሲሆን እንደ ቲማቲም፣ ጎመን፣ ሰላጣ፣ ካሮት፣ ወዘተ በግቢዎቻቸው ባሉ ክፍት ቦታዎች፣ በቤታቸዉ ዙርያና በአጥር ግድግዳ በባልዲ ላይ ጭምር አትክልት በማምረት ከራሳቸዉ ፍጆታ አልፈዉ ለሽያጭም የሚያቀርቡ የከተማ ነዋሪዎች ብቅ እያሉ ነዉ።
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU