• Call Us
  • +25146 554 16 87

የቢሮው ስልጣንና ተግባር

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣ አዋጅ ቁጥር 199/2015 መሠረት የግብርና ቢሮ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ተሰጥተውታል፡፡

O የግብርና ልማትን ለማስፋፋት የግብርና እና የእንስሳት ግብዓቶችን ማባዣ፣ የዕፅዋት እና የእንስሳት ጥራት ቁጥጥር ማዕከላትን፣ ማሰልጠኛ ተቋማትንና     ላቦራቶሪዎችን ያቋቁማል፣ ያስፋፋል፣

O በግብርና፣ በእንስሳትና በአሳ ልማት ኢንቨስትመንት ዘርፍ ለተሰማሩና ለሚሰማሩ ባለሀብቶች እና ባለድርሻ አካላት መረጃና የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል፣

O የግብርናውንና የእንስሳት ዘርፍ ምርትና ምርታማነት ለማሻሻል ለአርሶ አደሩ፣ ለአርብቶ አደሩ እና ለግል ባለሀብቱ የሚሰጡ የኤክስቴንሽንና የሥልጠና   አገልግሎቶች እንዲስፋፉ ያደርጋል፣

O የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠናው ኮሌጆችን ያስተዳድራል፣

O የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ከክልሉ የሰው ኃይል ፍላጎት ጋር መጣጣሙን ያረጋግጣል፣ ስልጠናው ፍላጎትን መሰረት ያደረገ እንዲሆን ያደርጋል፣

O የግብርና፣ የእንስሳት እና አሳ ግብዓት አቅርቦት፣ ስርጭትና ግብይት አቅምን ይገነባል፣ የብድር አቅርቦትና ስርጭት ያመቻቻል፣ ያረጋግጣል፣

O የግብርና፣ የእንስሳትና አሳ ምርት ግብዓት ወይም ግብዓት ብዜት ዘርፍ ለሚሰማሩ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ይሰጣል፣ይቆጣጠራል፣   በሕግ መሰረት ይሰርዛል፣

O የግብርና፣ እንስሳትና አሣ ኤክስቴንሽን መርሃግብር ያዘጋጃል፣ ስትራቴጃዎችና ስልቶችን ይቀይሳል፣ ይተገብራል፣ የኤክስቴሽን ስርዓቱን በማጥናት እንዲሻሻል   ያደርጋል፣

O አርሶ አደሮች በህብረት ስራ ማሕበራትና በግል ባለሀብቶች አማካይነት የሚካሄዱ የዘር ብዜት ስራዎች እንዲስፋፉ ያደርጋል፣ ያስተባብራል፣ የቴክኒክ ድጋፍና   የምክር አገልግሎት ይሰጣል፣

O ሕገ-ወጥ የግብርና፣ የእንስሳትና የአሣ ግብዓቶች ግብይትና ዝውውር ይቆጣጠራል፣ ይከታተላል፣ በሕግ መሰረት እርምጃ ይወስዳል፣

O  የግብርና፣ የእንስሳትና የዓሣ ልማት ባለሙያዎችን መልምሎ ያሰለጥናል፣ የአርሶ አደሮች የስልጠና ማዕከላትን ያቋቁማል፣ ያስተዳድራል፣

O ከአጎራባች ክልሎች ወደ ክልሉ የሚገቡ የእንስሳት፣ እፅዋት፣ የአዝርዕት እና ተዋፅኦ ላይ ተገቢውን ቁጥጥር ያድርጋል፣

O በክልሉ የሰብል ሃብት ላይ ወረርሽኝ እንዳይከሰት  ይከላከላል፣ ከተከሰተም በአፋጣኝ በቁጥጥር ስር እንዲውል ያደርጋል፣

O በግብርና ምርት እና በእንስሳት ሃብት ላይ ተፅዕኖ የሚያስከትሉ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ይከታተላል፣ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ይዘረጋል፣ አፋጣኝ እርምጃ     ይወስዳል፣

O የሰፈራ ፕሮግራም በበላይነት ይመራል፣ ሰፋሪው እስከሚቋቋም ድረስ አስፈላጊ የሆኑ የእርሻ መሳሪያዎች፣ ግብዓትና መሰረተ ልማቶች እንዲሟሉ ያደርጋል፣

O የግብርና ምርቶች ግብዓት እና የእንስሳት ሃብት ልማት አስፈላጊ መሰረተ-ልማቶች ይገነባል፣ እንዲገነቡና እንዲስፋፉ ያደርጋል፣

 O የክልሉን አጠቃላይ የግብርና እና የእንስሳት ግብዐትና የአደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ ያሰባስባል፣ ያጠናቅራል፣ይተነትናል ለሚመለከታቸው አካላት     ያሰራጫል'

O  ግብርና፣ የእንስሳትና የአሣ ሃብት ምርምር ዓቅም ይገነባል፣ የምርምር ውጤቶችን ያሰርፃል፣ የምርምር ባለድርሻ አካላት በቅንጅትና በትብብር የሚሰሩበትን   ስርዓት   ይዘረጋል፣

 O የሰብል ሃብት ልማት እንዲስፋፋ ያደርጋል፣ ተስማሚ ፖኬጆችን ያዘጋጃል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣

  O የግብርና ምርት፣ የእንስሳትና ዓሣ ልማት ግብዓት ጥራት አጠባበቅ ለአምራቾችና ለሌሎች ተዋንያን የምርምር አገልግሎትና ስልጠና ይሰጣል፣ የግብዓቶች ጥራት    ቁጥጥር  ያደርጋል፤

O  በክልሉ በሰው ሰራሽ ወይም በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን በቋሚነት መልሶ ለማቋቋም የሚረዱ የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክቶች አጥንቶ     ያቀርባል፣ ሲጸቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣

O  በዕለት ዕርዳታ ስራ ላይ ከሚንሳቀሳቀሱ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በጋራ ይሰራል፣ አሰራራቸውን በበላይነት ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣

 O የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ስራዎችን ያከናውናል፣

 O በገጠር ለምግብ ዋስትና ችግር የተጋለጡ አካባቢዎችንና የኀብረተሰብ ክፍሎችን ይለያል፣ መንስኤውን ያጠናል፣ ይደግፋል፣ በዘርፉ የሚሠሩ ባለድርሻ አካላትን   ያስተባብራል፣

O ዘላቂ የግብርና ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችል የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ስራዎች ያከናውናል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፣

O የጥቃቅንና የአነስተኛ መስኖ ልማት እንዲስፋፉ አግባብ ካለው አካል የተጠኑ ጥናትና ዲዛይን መሰረት በማድረግ ግንባታ እንዲካሄድ ያደርጋል፣ አቅርቦቱንም   ይደግፋል፣  

O የግብርና ምርምር አቅም ይገነባል፣ ባለድርሻ አካላት በቅንጅትና በትብብር የሚሰሩበትን ስርዓት ይዘረጋል፣

O የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ምርትና ምርታማነት ለማሻሻል የእንስሳትና ዓሳ ዝርያ ብዜት ስርዓት ይዘረጋል፣ ይተገብራል፣ አገልግሎቶች ይሰጣል፤ እንዲስፋፉ   ያደርጋል፤

O የእንስሳት ክትባትና መድሐኒት አቅርቦት፣ ግብይት፣ አያያዝ ዝውውር ስርዓት ይዘረጋል፣ የብቃት ማረጋገጫ ይሠጣል፣ ይቆጣጠራል፣ በህግ መሠረት እርምጃ     ይወስዳል፣

O የእንስሳት ገበያና የዝውውር መስመሮችን ይወስናል፣ ይቆጣጠራል፣ የኳራንቲይን አገልግሎት ይሰጣል፣ ከአጎራባች ክልሎችና ከፌዴራል መንግሥት አካላት ጋር   በቅንጅትና ትብብር ይሠራል፣

O የእንስሣት በሽታ ወረርሽኝና ተዛማች በሽታዎች እና የውሃ አካላት ብክለት የመከላከያና የመቆጣጠሪያ ሥርዓት ይዘረጋል፣ ያስፈጽማል፣ ሲከሰትም አፋጣኝ   እርምጃ   ይወሰዳል፣

O የእንስሳት የጤና አገልግሎት ይሰጣል፣ የእንስሳት በሽታዎች ምርመራ፣ አሰሳና ቁጥጥር ሥራዎችን ያካሄዳል፣

O የእንስሳትና ዓሳ ሀብት በልማት ቀጠናዎች ይለያል፣ እንዲለማ ተገቢውን ድጋፍ ያደረጋል፣

O በክልሉ ለሚገኙ ቄራዎችና የእርድ ቦታዎች የቁም እንስሳትና የበድን ስጋ ምርመራና ቁጥጥር ያደርጋል፣ መስፈርቶችን ያዘጋጃል፣ ተግባራዊነታቸውን ይቆጣጠራል፣   ባለሙያ ይመድባል፣ ደረጃቸውን ያልጠበቁትን ይዘጋል፣ አስፈላጊ እርምጃ በሚመለከተው አካል እንዲወሰድ ያደርጋል፣

O ዓላማውን ለማሳካት የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡