• Call Us
  • +25146 554 16 87

የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ

                           የእንስሳትና ዓሳ   ሀብት ልማት ዘርፍ ተጠሪነቱ ለግብርና ቢሮ ሀላፊ ሆኖ የሚከተለውን ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል፡-

O የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍን ምርታማነት ለማሻሻል ለአርሶ አደሩ፤ለግል ባለሀብቱና በእንስሳት ልማት ለተሰማሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጡ     የኤክስቴንሽንና የስልጠና አገልግሎት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤

O የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማትን የሚያፋጥን የፖሊሲ፣ የስትራቴጂና ፕሮግራም ሀሳቦችን በማመንጨት እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ሲፈቀድም እንዲተገበሩ ደርጋል፣   ይመራል፤

O የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት እና የአየር ንብረት ለዉጥ መቋቋሚያ አሬንጓዴ ኢኮኖሚ ተመጋጋቢነት እንዲጎለብት ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ ተግባራዊነቱን   ይከታታላል፣ ይመራል፤

O የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍን ለማዘመን የሚረዱ ዕውቀትና ክህሎትን ለማሻሻል የሚያግዙ ስልጠናዎች እንዲሰጡ ያደርጋል፣ የስልጠና ማዕከላት/የልህቀት   ተቋማትን እንዲቋቋሙ ያደርጋል፣ ይመራል፤

O የተፈጥሮ ግጦሽና በመስኖ የሚካሄድ የመኖ ልማት፣ የደረቅና ዕርጥብ መኖ ባንኮችን ያስፋፋል፣ የሚገኘውን ጠቀሜታ ይገመግማል፣ግብረመልስ ይሰጣል፣

O የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ተገቢውን የጤና አገልግሎት ማግኘታቸውን ያረጋግጣል፣ መከላከልን መሰረት ያደረገ የጤና ኤክስቴንሽን ለአርቢው እንዲሰጥ   ያደርጋል፤

O በየግብርና ለሴቶችና ወጣቶች የስራ ዕድል እንዲፈጠሩ ስርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ ይመራል፤

O ለእንስሳት ሀብት ልማት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚረዱትን የእንስሳት ዝርያና የመኖ ዕፅዋት ዘር ብዜትና ሥርጭት ተቋማትን የማቋቋሚያ ሐሳብ   ያቀርባል፣ ሲጸድቅም ይተገብራል፤

O ዘርፉ ከስሩ የሚከተሉት ዳይሬክቶሬቶችን  ያስተባብራል፡-

                o. የመኖ ልማት ዳይሬክቶሬት

                 o. የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት

                 o. የእንስሳት ጤናና ቬትረነሪ ዳይሬክቶሬት