CERS-Bureau of Agriculture
የ5-10-25 የዶሮ ልማት ፕሮጀክት (ያልተደረሱትን መድረስ)
በገጠርም ሆነ በከተማ የተሻሻለ ዝርያ ዶሮ የሌለው ቤተሰብ አይኖርም በሚል እሳቤ፤ ለአንድ ዝቅተኛ ገቢ ላለው ቤተሰብ ቢያንስ 5 ዶሮ፤ ትንሽ ሻል ላለው 10፤ ከፍ ላለው ደግሞ 25 ዶሮዎች እንዲኖሩት ይሰራል የሚል ኢኒሼቲቭ ነው። የኢኒሼቲቩ መነሻ የብልፅግናን አካታችነት በተግባር ለማረጋገጥ አጋዥ አቅም መሆኑን ማሳያ ነው። ከ25 በላይ የተሻለ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ያሉ ሁሉ ሊሰሩት የሚችሉት ስለሆነ አቅም የሌላቸው እንዳይገለሉ ያደርጋል። በዚህ መሰረት ከፍተኛ የመልማት አቅም ያላቸውን ወረዳዎች፣ ቀበሌዎችንና መንደሮችን በመምረጥ በዶሮ ልማት መንደር በማደራጀት የአርሶ አደሮችን የሴቶችንና ወጣቶችን ፍላጎት መሰረት ባደረገ መልኩ 5፡10፡25 ዶሮዎችን በኩታ ገጠም ማርባት የተጀመረ ሲሆን እስካሁን 278 መንደሮች እንዲሁም በከተማ ዘመናዊ የዶሮ እርባታ አሰራር በ5 ከተሞች ስኬታማ ስራ ተሰርቷል፡፡ ይህ ፕሮጀክት የብዙ አቅመ ደካማ ቤተሰቦችን ቀልብ ስቧል፣ተጠቃሚም ሆነዋል።
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU