• Call Us
  • +25146 554 16 87

የቢሮ ኃላፊ አማካሪ

       የቢሮ ሀላፊ አማካሪ ተጠሪነቱ ለቢሮው ሀላፊ ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-

O በመንግስት የወጡ ልዩ ልዩ የልማትና የምርምር ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች አፈጻጸም ዝርዝር ጥናት እያጠኑ ከተቋሙ ተግባርና ኃላፊነት አንጻር በመገምገም ሀላፊውን ያማክራል፤

O ስለ መንግስት የስራ አመራር እና ተቋሚ ለውጥ የሚወጡ ደንቦችና መመርያዎች በመተንተን የተቋሙ የሀብት ሥራ አመራር የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማሣደግና ለማሻሻል የሚያችል ጥናት ያካሄዳል፣

O በሴክተሩ የስትራቴጂክ የአካባቢ ግምገማ (Strategic Environmental Assessment) ፖሊሲዎች፣ ፕሮግራሞችና ዕቅዶች ሊኖራቸው የሚችለውን የረዥም ጊዜ አጠቃላይ አካባቢያዊ ተፅዕኖን ያጠናሉ፣ ያማክራሉ፤

O በተቋሙ አፈጻጸም ዙሪያ የውጭና የውስጥ ህጎችን፣ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችን፣ መመሪያና ከደንቦች ጋር በማገናዘብ ያማክራሉ፤ ውሳኔ የሚጠይቁ ጉዳዮችን በመለየት ከአስተያየት ጋር ያቀርባሉ፤

O ፖሊሲ፣ ስትራቴጅዎች እና ሌሎች ህጎች ላይ ጥልቅ ትንተና ያደርጋል፤

O የቢሮ ሀላፊው በፕሬስ ሪሊዝ፣ ፕሬስ ኮንፍረንስ፣ በቃለ ምልልስ፣ በሚዲያ በሚያስተላልፈው መግለጫዎች ላይ አስፈላጊውን የማማከር ሥራ ይሠራል፣ በጽሁፍ አዘጋጅቶ ያቀርባል፤

O የቢሮው ዓላማ ለመደገፍ የሚችሉ የልማት ፕሮጀክቶች ስምምነቶች ከመፈረማቸው በፊት ከመንግስት ፖሊሲ ጋር የተጣጣሙ መሆናቸው፣ ቴክኒካዊ ብቃታቸውና የሚያበረክቱት ጥቅም በመገምገም እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር በመመካከር የውሳኔ ሀሳብ በማቅረብ ሀላፊውን ያማክራል፤

O ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች/አካላት ጋር በመተባበር በውይይት/ወርክ ሾፕ/ ሴሚናር/ መድረኮች ላይ መቅረብ የሚገባቸውን ጉዳዮች አጠናቅሮ ያቀርባል፤

O የሥራ ክፍሎች እቅድ ተጣጣሚነት ያለው ሆኖ እንዲዘጋጅ፣ እንዲተገበርና የአፈጻጸም ውጤታማነቱም ወጥነት እንዲኖረው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ ይሠራል፤

O ከዞንና ልዩ ወረዳ ካሉ የየግብርና መስሪያ ቤቶች መካከል ጤናማ ተደጋጋፊ የሥራ ግንኙነት እንዲፈጠር ለማድረግ የሥራ ሂደቶች በሚያቀርቧቸው ጥናቶች ወይም ንድፈ ሃሳቦች ላይ ሙያዊ አስተያየት በመስጠት ያቀርባል፣

O ከተጠሪ ተቋማት፣ ከባለድርሻ አካላትና ተገልጋዮች የሚቀርቡ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ከመንግስት ፖሊሲና የልማት አቅጣጫ አንጻር እያጠና የፖሊሲ ትንታኔና ማብራሪያዎች ያዘጋጃሉ፤

O በተቋሙ አሠራርና አስተዳደር ዙሪያ የተጻፉ ወቅታዊ ጽሁፎችን፣ በመተንተን እና ከክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ሊሻሻሉ ወይም ሊለወጡ የሚገባቸው አሠራሮች ወይም አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ አስተያየትና የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባሉ፤

O አግባብ ካላቸው ሙያተኞች ጋር በመተባበር የተቋሙን ተልዕኮ በሚመለከት የሚደርጉ የሁለትዮሽ/ሶስትዮሽ ግንኙነት፣ የመግባቢያ ስምምነት ላይ ተገቢውን ጥናት በማድረግ ስምምነቱ ከመፈረሙ በፊት የተዘጋጀውን ሰነድ በመመርመር ሀላፊውን ያማክራል፣ ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጋር በመሆን የስምምነት ሰነድ አዘጋጅተው ያቀርባሉ፤