CERS-Bureau of Agriculture
የ10 በ25ሜ, 20 በ 25ሜ እና 20 በ 50ሜ የተሸሻለ መኖ ልማት ፕሮጀክት፡
100ካሜ፣ 250 ካሜ፣ 500 ካሜ፣1000 ካሜ በሆነ ማሳ በቤተሰብ ደረጃ በተሻሻለ መኖ ልማት በመሳተፍ የእንስሳት መኖ አቅርቦት ለማሳደግ ማልማት ነው። ይህ ማለት አንድ ቤተሰብ ከሶስቱ አማራጮች እንደአቅሙ አንዱን ተጠቅሞ ያለማል። ማለትም (250 ካሜ፣ 500 ካሜ እና 1000 ካሜ) የእንስሳት መኖ በቤተሰብ ደረጃ የማልማት ኢኒሼቲቭ ነው። በተመሳሳይ ይህ ፕሮጀክት አንድ ቤተሰብ በትንሹ ከአንድ እስከ ሁለት የተሻሻለ የወተት ዝርያ ጊደር/ላም የሚኖረው ሲሆን ይህ ፕሮጀክት ለአንድ ቤተሰብ ከ250 -1000 ካሜ ቦታ መኖ ያለማል ማለት ነው። መኖ ለእንስሳቱ እና ለአልሚው ቢዝነስና ገቢ ብሎም ስራ እድል ጭምር መፍጠሪያ እንዲሆን ተቀርፆ እየተተገበረ ያለ ፕሮጀክት ነው። እስካሁን በርካታ ውጤቶች የተመዘገበበት ኢኒሼዬቲቭ ሲሆን በ2015/6 ም/ዘ በበልግና መኸር ወቅት 234,334 አርሶ አደሮች በቤተሰብ ደረጃ ኩታገጠም በሆነ መልኩ ከ250 -1000 ካሜ መሬት የተለያዩ ማልሚያ ስልቶች ተጠቅሞ እንዲያለማ በመደገፍ 106,277 ሄ/ር መሬት በመሸፈን ተደማሪ ውጤትና ስኬት እንዲመጣ ያደረገ ኢኒሺዬቲቭ ነው፡፡ በተመሳሳይ የመንግስትና የግል ተቋማት በመኖ ልማት እንድሳተፉ በማድረግ በ354 ትምህርት ቤቶች 531ሄ/ር መሬት መኖ እንዲያለሙ በማድረግ፣ በክልሉ በተገነቡ በመስኖ አወታሮች ከሰብል ልማት ጋር በማቀናጀት ከ200 ሄ/ር ማሳ በማልማት የመኖ ሽፋን እንዲሰፋና አቅርቦቱ በማሳደግ የእንስሳት ተዋፅኦ ምርት እድገት ላይ የማይናቅ አስተዋፅኦ እያደረገ ያለ ውጤታማ ስልት ነው፡፡
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU