CERS-Bureau of Agriculture
የግብዓት አቅርቦት ዘርፍ ተጠሪነቱ ለግብርና ቢሮ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፤
O የግብዓት አቅርቦት ስርዓት ክትትል በማድረግ እና ግብይት ስርዓት ፖሊሲዎችንና ፕሮግራሞችን በጥናት ላይ ተመስርቶ ይቀርጻል፣ ውሳኔ ሲያገኝ ተግባራዊ ያደርጋል፤
O የግብዓት አቅርቦቱ ለአርሶ አደሩ በመጠን፣ በጥራትና በዓይነት ተደራሽ እንዲሆን ጥናት ያደርጋል፤
O በግዥ የሚቀርቡ ግብዓት እና ስርጭት ተግባር ላይ የተሳተፉ እና ለመሳተፍ የሚፈልጉ አካላትን የአቅም ግንባታ ስራ ይሰራል፤
O ጥራትና ደረጃው የተጠበቀ ግብዓት ለአርሶ አደሩና፣ ለባለሀብቶችና የተደራጁ የማህበረሰብ አካላት እየቀረበ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ይከታተላል ችግር ያለባቸውን O በመለየት ለበለጠ ሙያዊ ጥራት ቁጥጥር ለሚመለከታቸው ላቦራቶሪ እንዲያሳወቁ ያደርጋል አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
O የግብዓት አመራረት፣ ክምችት፣ የአጓጓዝ ሂደት በሥርዓት እንዲመራ የአሰራር ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል ፡፡
O ከምርምር ማዕከላትና ከግብዓት አቅራቢ ማዕከላት ጋር የቅርብ ግንኙነት በመፍጠር ተፈላጊ የስነ- ህይወታዊ ግብዓት ምርት ግብዓት ውጤታማ የሆኑ በምርምርና በጥናት እንዲቀርቡ በቅንጅት ይሰራል ፣
O ለምርምር በሚቀርቡ ሃሣቦች/ የምርምር ኘሮፖዛሎች/ ላይ በሚደረግ ውይይት በመሳተፍ የበኩሉን አስተያየት ያቀርባል፣
O የግብዓት ጋር የተገናኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ያዘጋጃል፣ ያፀድቃል፣ አተገባበራቸውንም በመከታተል ሪፖርት ያቀርባል፣
O በግዥ የሚቀርቡ ግብዓቶች ፍላጎት ትንበያ፣ እና ስርጭት ዙሪያ ለአቅራቢዎች እና ተጠቃሚዎች ምቹ እንዲሆን አዳዲስ የአሰራር ሥርዓት ስለሚሻሻልበት ሁኔታ ሀሳቦችን ያቀርባል፤ይዘረጋል፡፡
O በግብዓት ሥርጭት ዙሪያ ከተለያዩ አካባቢዎች የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
O ቅንጅታዊ አሠራር ለማጎልበትና ለማጠናከር የሚያስችሉ ስልቶችን በመቀየስ በወቅቱ ግብዓት ለአርሶ አደሩ/አርብቶ አደሩ እንዲደርስ ያደርጋል፤
O ኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ መንግስታዊ የልማት ድርጅቶችና ልማታዊ ባለሀብቶች በግዥ የሚቀርቡ ግብዓቶችና ሥርጭት ላይ እንዲሳተፉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
O ግብዓቶች ተገዝተው ከመቅረባቸው በፊት ተገልጋዮች ዝግጅት እንዲሁም የቅበላ አቅም በመገምገም ዝግጁ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ የዝግጅት ክፍተት ሲኖር የማሟያ ስልት ይነድፋል፣
O በአከባቢው የሚተገበሩ የተፋሰስ ልማትና ከሌሎች የግብርና ልማት ሥራዎች ጋር በተቀናጀ መልኩ የግብርና ግብዓት እና ስርጭት ለማስፋፋት የሚያስችሉ አዳዲስ የውጤቶችና የተሸሻሉ አሰራሮች በማሰባሰብ ለቴክኒክ አሰራር ዝግጅት ግብዓት ደርጋል፤
O ተገቢ የግብርና ሜካናይዜሽን ምንጮችን የግዥ ስልት፣ እቅድ ፣ፖሊሲ፣ አሰራርና፣ መመረያዎችን መፈተሽና ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፤
O የግብርና ሜካናይዜሽን ከጠቅላላው የግብዓት ስልት አንጻር በመቅረጽ ይመራል፤
O ግዥ፣ ማከማቸትና ማሰራጨት የሥራ እንቅስቃሴዎች የጥራትና ብቃት፣ የዋጋ ተወዳዳሪነት እንዲሁም የላቀ አገልግሎት ለውስጥና ለውጭ ተገልጋዮች ከመስጠት አንጻር ያለውን እንቅስቃሴ በመፈተሽ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
O የተፋሰስ ልማት በሚካሄድበት አከባቢ የሜካናይዜሽን ግብዓት ሥራዎች ያሉበትን ደረጃና ችግሮችን ለመፍታት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት መነሻ የሚሆኑ መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ ይለያል፤
O የሜካናይዜሽን ግብዓት መረጃዎችን የማደራጀት፣ ለዘመናዊ መረጃ ቋትና ፣ለዕቅድ ዝግጀት ያመቻቻል፤
O የሜካናይዜሽን ግብዓት ሥራ በአከባቢው ያለበትን ደረጃና የህበረተሰቡን ልማዳዊ አሠራር በመለየት የተሰበሰቡ መረጃዎችን መሠረት በማድረግ ትንታኔ መስጠት፣ በአግባቡ ያደራጃል፤
O በአከባቢው የሚተገበሩ የተፋሰስ ልማትና ከሌሎች የግብርና ልማት ሥራዎች ጋር በተቀናጀ መልኩ የሜካናይዜሽን ግብዓት ለማስፋፋት የሚያስችሉ አዳዲስ ውጤቶችና የተሸሻሉ አሰራሮች በማሰብሰብ ለቴክኒክ አሰራር ዝግጅት ግብዓት ያደርጋል፤
O የሜካናይዜሽን ግብዓት በተመለከተ ለሚዘጋጁ የአጭር ጊዜ ፕሮጀክቶች፣ አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን፣ ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች መረጃዎችን ያሰባስባል፤
O የግብርና ሜካናይዜሽን ግብዓት በሚመለከት በተዘጋጀው የስልጠና ሰነድ መሰረት ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠና ይሰጣል፤
O በተፋሰስ ልማት ተግባራዊ የሚደረጉ የሜካናይዜሽን ግብዓት ሥራዎች በተዘጋጀው ዕቅድና መመሪያ መሰረት እንዲከናውኑ ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት ይከታተላል፤
O ዘርፉ ከስሩ የሚከተሉት ዳይሬክቶሬቶችን ያስተባብራል፡-
o. የግብርና ሜካናይዜሽን ዳይሬክቶሬት
o. ግብርና ግብአት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU