CERS-Bureau of Agriculture
የክልሉ ግብርና ቢሮ የህዝቡን ኢኮኖሚያዊ እድገትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተለይም የአርሶ አደሩን ገቢና ኑሮ ለማሻሻል መጠነ ሰፊ ርብርብ ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች መካከል የሰብልና የእንስሳት ምርትና ምርታማነት ማሳደግ መሆኑን ታወቃል፡፡ በመሆኑም እነዚህ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ሊደግፉ የሚችሉ በርካታ የግብርና ሴክተር አዳዲስ ኢኒሼቲቮች በክልሉ በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና በቢሮው ሃላፊ በተከበሩ አቶ ኦስማን ሱሩር ስራጅ ሀሳብ አመንጪነትና መሪነት ተቀርፀው ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን በአንድ በተመረጠ መልካዓ ምድር ውስጥ የገበያ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ፣ ለክልሉም ሆነ ለአገሪቱ ስትራቴጅክና አዋጭ የሆኑ ምርቶች ላይ ቅድሚያ በመስጠት፣ ተመሳሳይ የግብርና ምርት አይነቶች ኩታገጠም በሆነ መልክ በስፋት የሚመረቱበትንና ጥራታቸውን ጠብቀው ለገበያ ሊቀርቡ የሚችሉበትን ታሳቢ ያደረገ የአሰራር ሥርዓት ተዘርግቷል፡፡
የአዳዲስ ኢኒሺዩቲቮቹ አተገባበር በተመለከተ የክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ያላቸውን ሀብትና ዕምቅ አቅም መሠረት በማድረግ የልማት መንደሮች በመለየት በአካባቢያዊ ተስማሚነት እና በገበያ ተፈላጊነታቸው የተመረጡ የግብርና ምርቶች ማሳደግ ላይ በማተኮር ወደ ተግባር በማሸጋገር ሊገኝ የሚችለውን ጥቅም አሟጦ ለመጠቀም የሚረዳ የአተገባበር ስልት ነው፡፡ መንደርን መሰረት ያደረገ ድጋፍ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያቶች የተለዩ ሲሆን በተለይም ተመሳሳይ የምርት ማሻሻያ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች በአንድ አካባቢ ወይም በመንደር ማደራጀት ለክትትል አመቺ ከመሆኑም በላይ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን የሥራ አዋጭነት ለመገምገምና የማሻሻያ ሀሳቦችን ለማቅረብ አመቺ በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህም በላይ የቴክኖሎጂ ሥርፀቱን በአጭር ጊዜ ለማስፋፋት ተጠቃሚ አርሶ አደሮችና በዚህ ተመሳሳይ ሥራ ለሚሳተፉ ግለሰቦችን በአንድ አካባቢ ማግኘት ቴክኖሎጂው በፍጥነት እንዲታወቅና የተሳታፊ አምራቾችም ብዛት እንዲጨምር ይረዳል፡፡ በሂደትም የመንደሮች ስብስብ ክላስተሮችን በመፍጠር፤ የክላስተሮች ስብስብ ኮሪደሮችን እንዲፈጥር ታስቦና ታቅዶ የተዘጋጀ ነው። በተጨማሪም ለምግብ ዋስትናችን ወሳኙን ድርሻ እንዲይዝ ለሚደረገው ጥረት አጋዥ እንዲሆን ታስቦ እንደየ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ለአተገባበር በሚያመች መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን የተዘጋጀ ስልት ነው፡፡ የተያዘውን ፕሮግራም ለማሳካት አ/አደሮች በየመንደራቸው በተመረጠ ኢኒሺዩቲቭ ለመሳተፍ ሙሉ እምነት ያላቸው፣ ሰልጥነው በተገቢው ሁኔታ መተግበር የሚችሉ፣ የሚያስፈልጉ ቴክኖሎጂዎችን ጥንቅሮች በማሟላት ወደ ስራ ሊገቡ የሚችሉ፣ ፈጣን የኤክስቴንሽን አገልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑ በግላቸውም በየጓሮአቸው ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ ማንኛውም ሰው መሳተፍ የሚያስችል ነው፡፡ በአንድ መንደርም ቢያንስ ከ100 እስከ 120 አርሶ አደር እንዲሳተፍ የታቀደ ነው፡፡ በዚህ አሰራር ስልት መሰረት የሚተገበሩ በዋና ዋናና በተመረጡ ምርት አይነቶች ኢኒሺዮቲቮች በመቅረፅ በተመረጠ የምርት መንደርን መመስረት መሰረት ያደረጉ ሲሆን በተመረጡት መንደሮች አካባቢ ለሚገኙ አ/አደሮች ልዩ ድጋፍ ለመስጠት ሲታቀድ በዋናነት የፍራፍሬ መንደር፣ የዶሮ መንደር፣ የቅመማ ቅመም መንደር፣ የንብና ማር ልማት መንደር፣ የወተትና የእንስሳት መኖ ልማት መንደር፣ የከተማ አትክልት መንደር በሚል የተጀመረ ስራ ነው።
የኢኒሺዩቲቮቹ ተደማሪ ስኬትና አተገባበራቸው
ስራው በ2014 በቅድሚያ በተወሰኑ አካባቢዎች በመጀመር በመቀጠልም በሌሎች በተለዩ መንደሮች እንደየ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ በማስፋፋት ወደ ውጤት የተቀየረ ነው፡፡ በዚህ መሰረት በክልሉ ወደ ስራ የገቡና ተጨባጭ ውጤት የተመዘገገባቸው ስምንት(8) ኢኒሼቲቮች ዝርዝርና ያስገኙት ፋይዳ ከስር በዝርዝር ቀርቧል፡፡
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU