CERS-Bureau of Agriculture
የ3-7 ፕሮጀክት (3-7 የፍራፍሬ ዛፍ ለአንድ የከተማ ነዋሪ) ፡-
ዓላማውን የምግብ ፍጆታ ፍላጎትን በከተማ አካባቢ ለማማሏት ያደረገው ይህ የከተማ የግብርና ልማት ስራ የተከሠተውን የኑሮ ውድነት ለማስታገስ የምርት ፍላጎትን እና አቅርቦትን ለማጣጣም የከተማ ግብርና በተለይም ፍራፍሬ ልማት ወሣኝ መሆኑን በመረዳት ወደ ትግበራ መግባት አስፈላጊ መሆኑን ታምኖበት ይህ ኢኒሺዩቲቭ ተቀርጾ ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን በሁሉም ከተሞች በመተግበር ውጤት የተገኘበት ነው፡፡ በተለይም በከተማ ክልል የሚገኝ ማህበረሰብ በውስን ቦታ ሰብል የማልማት ፍላጎት በአመለካከትም በክህሎትም እየተለመጠ መሆኑን፣ ከፍራፍሬ ምርት ገቢ በማግኘት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባሻገር ስነ-ምህዳራዊ ፋይዳውም መረዳቱ፣ የተተከሉ ፍራፍሬዎች ለመኖሪያ ስፍራ ውበትና ጥላ በመሆን የቤተሰብ መንፈስን የሚያድሱ ሆነው መታየታቸውና የየከተሞቹ አስፈፃሚ አካላት የተገልጋዩ ፍላጎት መነሻነት የግብርና ግብአቶች በተለይም ፍራፍሬዎች በማባዛት አቅርቦት ማመቻቸት መጀመራቸው ከሚጠቀሱ ፋይዳዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU