• Call Us
  • +25146 554 16 87

የግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር እና ኳራንቲን ባለስልጣን

 የግብርና ግብዓቶችን ጥራት ቁጥጥርና ኳራንቲን ባለስልጣን ተጠሪነቱ ለግብርና ቢሮ ሀላፊ ሲሆን የእጽዋት ዘር፣ ጸረ ተባይ ኬሚካል፣ የአፈር ማዳበሪያ፣ የተሻሻሉና አነስተኛ የእርሻ መሳሪያ ጥራት ቁጥጥር  እና የእጽዋት ኳራንቲን አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን የባለስልጣኑም የትኩረት መስኮች፡-

O የእጽዋት ዘር፣ ጸረ ተባይ ኬሚካል፣ የአፈር ማዳበሪያ፣ የተሻሻሉና አነስተኛ የእርሻ መሳሪያ  የጥራት  ቁጥጥር  በማድረግ  የጥራት ደረጃ ሟሟላቱን ማረጋገጥ፣

O በዘር ማምረት፣ ማዘጋጀት፣ በግብይት የተሰማሩ የግልና የመንግሥት ዘር አምራቾች ድርጅቶች እና በጸረ ተባይ ንግድ አቅራቢዎች፣ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መስጠት፣እና ማደስ፣

O ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ እንዲሁም ከክልሉ የሚወጡና ወደ ክልሉ የሚገቡ ተዛማች የሰብል በሽታ፣ ተባይ እና አደገኛ አረምን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል የኳራንቲን አገልግሎት መስጠት፣

O በእጽዋት ዘር ማምርት፣ ማዘጋጀት፣ ግብይት ለተሰማሩ የግልና የመንግስት ዘር አምራች ድርጅቶች እና የጸረ ተባይ ኬሚካል ቸርቻሪዎች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ይሰጣል፣ ያድሳል

O ለመንግስት፣ ለግልና ለሌሎችም አካላት የማሳ ላይ የዘር ጥራት ቁጥጥር ያደርጋል፣

O ከዘር መጋዘን ወካይ ናሙና በመዉሰድ የላቦራቶሪ ምርመራ በማድረግ የጥራት ማረጋገጫ እና የመለያ ምልክት (ታግ) ይሰጣል፡፡

O የግብርና ግብዓት ፍላጎትንና የዝውውር መስመሮችን መሰረት በማድረግ የዘር ጥራት ተቆጣጣሪ ላቦራቶሪዎችንና የኳራንቲን ጣቢያዎችን  ያቋቁማል፣ ያደራጃል፡፡

O በህገ ወጥ በሚዘዋወሩ ዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች የጫኑ ተሸከርካሪዎችን፣ ኮንተይነሮችንና ማከማቻ መጋዘኖችን ይፈትሻል፣ ይቆጣጠራል፣ እርምጃ ይወስዳል፡፡

O ማንኛዉንም ዘር ደረጃቸዉን ጠብቀው መመረታቸዉን ያረጋግጣል፤ ከጥራት ደረጃቸዉ በታች የሆኑትን ዘርና ሌሎች የግብርና  ግብዓቶች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ያደርጋል፡፡

O የግብርና ምርታማነታቸዉ የወረዱና ልዩ ባህሪያቸውን የለቀቁ ዝርያዎችን ከዘር ምርት እንዲወጡ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አብሮ በመስራት ድርሻዉን ይወጣል፡፡

O የግብርና ግብዓቶች የጥራት ደረጃዎችን መስፈርትና ደንብ የጣሱ ግለሰቦች ወይም ድርጅች ላይ አግባብነት ያላቸዉን የጥራትና የደረጃ ህጎችን መሰረት በማድርግ እርምጃ ይወስዳል፡፡

O በመስክና በክምችት የጥራት ቁጥጥር ተካሄዶባቸዉ የጥራት ደረጃ መስፈርቱን ያላሟላ ዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች አገልግሎት ላይ እንዳይዉሉ ያርጋል፡፡

O የዘር ጥራት ለማሻሻል የሚረዱ የምክርና የቴክኒክ ድጋፍ ለዘር አምራቾች፣ አዘጋጆች፣ ሸጮች እና አቅራቢዎች ይሰጣል፡፡

O በጸረ ተባይ ኬሚካል የግልና የመንግስት ነጋዴዎችን የጥራት ቁጥጥር መስፈርቱን ማሟላታቸዉን እያረጋገጠ የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ይሰጣል፡፡

O ባለስልጣኑ ሥራውን በአግባቡ ለመወጣት በስሩ የእፀዋት ዘር ጥራት ቁጥጥርና ኳራንቲን እና የግብርና ግብአቶች ጥት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬቶች ናቸው፡፡