CERS-Bureau of Agriculture
ህብረት ስራ ኤጀንሲ ተጠሪነቱ ለግብርና ቢሮ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት አለው፡-
O የተለያዩ ዓይነት መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበራትን፣ ኅብረቶችን (ዩኒየኖችን) እና ፌዴሬሽኖችን አግባብ ባለው ህግ እና በዓለም አቀፍ የኅብረት ሥራ መርሆዎች መሰረት ያደራጃል፣ ይመዘግባል፣ ሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፣
O የኅብረት ሥራ ማህበራትን የሥራ እንቅስቃሴ በመመዘን የሕጋዊ ሰውነት የምስክር ወረቀታቸውን ያድሳል፣ በአፈጻጸም ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑትን ያዋህዳል፣ እንዲከፈሉ ያደርጋል ይሰርዛል፣በሂደትም ሕልውናቸውን የሚያጡ ኅብረት ሥራ ማህበራትን በህግ አግባብ ከመዝገብ ይሰርዛል፣
O በባሕላዊ መንገድ የተደራጁ የራስ አገዝ ማሕበራት ወደ ዘመናዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት የሚያድጉበትን ጥናትና ምርምር ያደርጋል፣ ይተገብራል፣
O ስለኅብረት ሥራ እሴቶችና መርሆዎች አስፈላጊነት እና ጠቀሜታ ለህብረተሰቡ ቅስቀሳ ያካሄዳል፣ ትምህርት ይሠጣል፣ ግንዛቤ ይፈጥራል፣
O የኅብረት ሥራ ማኅበራትን የሂሣብ አያያዝና ምርመራ ሥርዓት ይዘረጋል፣ ኢንስፔክሽንና ኦዲት ያደርጋል ወይም ያስደርጋል፣ ሂሣብ አጣሪም ይመድባል፣ በህግ አግባብ ሲፈርስም ከመዝገብ ይሰርዛል፣
O ለኅብረት ሥራ ማህበራት የሕግ አገልግሎት ድጋፍ ይሰጣል፣ እንዳስፈላጊነቱ የኅብረት ሥራ ማህበራትን ወክሎ ይከራከራል፣
O የኅብረት ሥራ ማህበራት ባንክና ኢንሹራንስ እንዲያቋቁሙ ድጋፍ ይሰጣል፣ ለምዝገባ የሚያበቁ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ ይከታተላል፣
O የኅብረት ሥራ ማኅበራት በአባላት የግብርና ምርቶች ላይ አሴት በመጨመር የበለጠ የዋጋ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የግብርና ምርቶች ማቀነባበያ ኢንዱስትሪዎችን እንዲያስፋፉ ይደግፋል፣
O የዕዳ ጥበብ ኅብረት ሥራ ማኅበራት አባላት የእጅ ጥበብ ምርቶች እንዲያድጉ የሙያና የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል፣
O የኅብረት ሥራ ማኅበራት ቅድመና ድህረ የግብርና ሜካናዜሽን እንዲስፋፋ የማመከርና የመደገፍ አገልግሎት ይሰጣል፣
O የኅብረት ሥራ ማህበራት የግብርና ግብዓት አቅርቦትና ስርጭት ላይ እንዲሰማሩ፣ የምርት ጥራት ተጠብቆ የተሻለ ዋጋ እንዲያስገኙ ይደግፋል፣ ግንዛቤ ይፈጥራል፣ አቅም ይገነባል፣
O የኅብረት ሥራ ማኅበራት በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች በተለይም በኢንዱስትሪ እንዲሰማሩ ፕሮጀክቶችን በማጥናትና በማዘጋጀት ይደግፋል፣ የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ የሚያገኙበትን መንገድ ያመቻቻል፣
O የኅብረት ሥራ ማኅበራት ምርቶች ገበያ እንዲያገኙ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፣ ሸማቹና አምራቹ በቀጥታ የሚገናኙበትን ሁኔታ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፣ የምርት፣ የገበያ መረጃና የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ይደግፋል፣ የፋይናንስ፣ ግብዓትና የምርት ግብይት ትስሰር ይፈጥራል፣
O በህብረት ሥራ ማህበራት አማካይነት የቁጠባ ባህል በማዳበር በገጠርና ከተማ ቁጠባ እንድሰበሰብ ያግዛል፣ የአባላት ፋይናንስና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ ይደግፋል፣
O እንደየኅብረት ሥራ ማኅበራቱ ዓይነትና ደረጃ ሞዴል የመተዳደሪያ ደንብ ያዘጋጃል፣ ያሰራጫል፣ ይከታተላል፤
O በክልሉ የአፈር ማዳበሪያ፣ ምርጥ ዘርና አግሮ-ኬሚካል አቅርቦትና ስርጭት ይመራል፣ ሕገ-ወጥ የአፈር ማዳበሪያ ግብይትና ዝውውርን ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድም ያደርጋል፣
O የኅብረት ሥራ ማህበራትን በተሰማሩበት የስራ መስክ የብቃት ደረጃ ይለያል፣ የተሻለ የደረጃ ብቃት ያላቸውን ያበረታታል፣ ዕውቅና ይሰጣል፣
O ከኅብረት ሥራ ማኅበራት ጋር ግንኙነት ካላቸው መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በትብብርና በቅንጅት ይሰራል፣
O የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በራሱ ስም ይከሳል፣ ይከሰሳል
O ሥራው እየሰፋ ሲሄድ እንደአስፈላጊነቱ አንዳንድ የህብረት ሥራ ማህበራትን እንዲያደራጁ ለሌሎች ተቋማት ውክልና ሊሰጥ ይችላል፣
O ለኅብረት ሥራ ማህበራት አመራር አካላት፣ ቅጥር ሠራተኞችና ለአደራጅ መ/ቤቱ vለሙያዎች የአቅም ግምባታ ƒUI`ƒ“ eMÖ“ ይሰጣል፣
O ኅብረት ሥራ ማህበራት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የገበያ መሰረተ ልማት እንዲስፋፋ በጥናት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ ያደርጋል፣
O በኅብረት ሥራ ማህበራት አሰራር ዲጅታላይዝ እንዲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ሥርዓቱ እንዲዘረጋላቸው ያደርጋል፣
O ዓላማውን ለማስፈጸም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል የሚል ሥልጣንና ተግባራት አሉት፡፡
ኤጀንሲው የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
1. በኅብረት ሥራ ማኅበራት የመደራጀት ፍላጎትና እምቅ ሃይል ስለመኖሩ ደሰሳ ጥናት የማካሄድ አገልግሎት
2. በኅብረት ሥራ ማኅበራት ለመደራጀት ለወሰኑ የአዋጭነት ጥናት የማካሄድ አገልግሎት
3. ስትራቴጂክ እቅድና ቢዝነስ ፕላን የማዘጋጀት ድጋፍ አገልግሎት
4. የኅብረት ሥራ ማኅበራት ማደራጀት አገልግሎት
5. የኅብረት ሥራ ማህበራት የማዋሃድ፣ የማካፈልና የማፍረስ አገልግሎት፣
6. የቁጠባ ባህል የማዳበር አገልግሎት
7. የኅብረት ሥራ ማህበራትን በደረጃ የመለየት አገልግሎት
8. ልኬታዊ ኢንስፔክሸን አገልግሎት
9. የአማካሪ ቦርድ ማካተት አገልግሎት
10. የህግ ማዕቀፎች ዝግጅት አገልግሎት
11. የመስሪያ ቦታ እንዲመቻች የማገዝ አገልግሎት
12. ህጋዊ ሰውነት የመስጠት አገልግሎት
13. የአሰራር ሥርዓት ዝርጋት አገልግሎት
14. የሂሳብ ክትትል አገልግሎት
15. የአገር ውስጥ ገበያ ትስስር አገልግሎት
16. የግብርና ምርት ኤክስፖርት አገልግሎት
17. የግብርና ምርት ማሳደጊያ ግብዓቶች አቅርቦትና ሥርጭት አገልግሎት
18. የግብርና ግብዓትና ምርት ግብይት ብድር አቅርቦት የማመቻቸት አገልግሎት፣
19. የግብርና ግብዓትና ምርት ግብይት ብድር የማስመለስ አገልግሎት
20. የግብርና ምርት በጥራት እንዲዘጋጅ ምክር አገልግሎት
21. ምርትና አገልግሎታቸውን የማስተዋወቅ አገልግሎት
22. መሰረተ ልማት ግንባታ ሂደቶች የመደገፍና መከታተል አገልግሎት
23. የመጋዘን አስተዳደር አገልግሎት
24. የኢንስፔክሽን አገልግሎት
25. የኦዲት አገልግሎት
26. የብቃት ደረጃ ምዘናና ሰርተፊኬሽን አገልግሎት
27. የህግ አገልግሎት
28. የአማራጭ ግጭት አፈታት አገልግሎት
29. የአቅም ግንባታ ስልጠና አገልግሎት
30. የጥናትና ምርምር የማካሄድና የጥናቱን ውጤቱ የማስተዋወቅ አገልግሎት
31. የግብርና ሜካናዜሽን እንዲስፋፋ የማማከርና የመደገፍ አገልግሎት
32. የግብርና ኢንዱስትሪ እንዲስፋፋ የማማከርና የመደገፍ አገልግሎት
33. የኅብረት ሥራ ማህበራት የገበያ መረጃ ቴክኖሎጂ ሥርዓት ግንባታ አገልግሎት
34. የምርጥ ተሞክሮዎች ልምድ ልውውጥ የማመቻቸት አገልግሎት
35. የክትትልና ድጋፍ አገልግሎት
36. የምክር አገልግሎት
37. ከአቅም ገንቢዎች ጋር የማስተሳሰር አገልግሎት
38. የኅብረት ሥራ ማህበራትን ዲጅታላይዝ የማድረግ አገልግሎት
39. የኅብረት ሥራ ማህበራትን ሪፎርም የማድረግ አገልግሎት
40. ለኤጀንሲው የህግ አገልግሎት
41. መሰረታዊ መረጃ የማሰባሰብ፣ የማጠናቀርና ማሰራጨት አገልግሎት
42. ምርጥ ተሞክሮ መቀመር አገልግሎት
43. የፋይዳ ዳሰሳ ጥናት አገልግሎት
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU