CERS-Bureau of Agriculture
በም/ቢሮ ሀላፊ የሚመራ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ ተጠሪነቱ ለግብርና ቢሮ ሀላፊ ሆኖ የሚከተለውን ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል፡-
O የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍን ምርታማነትና ውጤታማነት ለማሻሻል ለአርሶ አደሩ፣ ለግል ባለሀብቱና በእንስሳትና አሳ ሀብት ልማት ለተሰማሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጡ የኤክስቴንሽንና የስልጠና አገልግሎት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
O የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍን ምርታማነትና ውጤታማነት የሚያፋጥን የፖሊሲ፣ የስትራቴጂና ፕሮግራም ሀሳቦችን በማመንጨት እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ሲፈቀድም እንዲተገበሩ ያደርጋል፤
O ለአነስተኛ አርሶ እና አርብቶ አደር መስኖ ልማት የሚውል የውሃ ሀብት እንዲለይና ጥቅም ላይ እንዲውል ስርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙንም ይመራል፣ ይከታተላል፤
O የተፋሰስና አግሮ ፎረስትሪ፣ የአካባቢና የአየር ንብረት ለውጥ የተሻሻሉ ዘመናዊ አሠራሮች ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙንም ይመራል፣ ይከታተላል፤
O የተፈጥሮ ሀብት ልማት ምርምሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር የሚሰሩበት ስርዓት ይዘረጋል፣ ሲፀድቁም እንዲተገበሩ ያደርጋል፤
O የተፈጥሮ ሀብት ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ተመጋጋቢነት እንዲጎለብት ስርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ ተግባራዊነቱን ይከታታላል፣ ይመራል፤
O የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍን ለማዘመን የሚረዱ ዕውቀትና ክህሎትን ለማሻሻል የሚያግዙ ስልጠናዎች እንዲሰጡ ያደርጋል፤
O የብዝሀ ሕይወት ሀብቶች በአግባቡ እንዲያዙ፣ እንዲጠበቁና የህብረተሰብ ጥቅም ተጋሪነት እንዲሰርጽ ይከታተላል፣የቅርብ አመራር ይሰጣል፤
O የአነስተኛ መስኖ ልማትንና የአነስተኛ መስኖ አውታሮች አስተዳደርና ውሃ አጠቃቀም ብቃት ለማሳደግና ለማጠናከር ፖሊሲዎችና መመሪያዎችን ማዘጋጀትና ማቅረብ፣ አዳዲስ የፖሊሲ ማሰፈጸሚያ ስትራቴጂዎችን ማመንጨት፣ ሲፈቀዱም ተግባራዊ ያደርጋል፤
O የማህበራዊ ምጣኔና የዘላቂ አካባቢያዊ ልማትን ሊያረጋግጡ የሚችሉ የመስኖ ውሃ መገኛ አካላትንና አማራጮችን ማጥናትና መረጃዎችን በተጠናከረ መልኩ ማደራጀት፣ መመርመርና መተንተን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን አፈጻፀማቸውን መከታተልና ሪፖርት ማድረግ፤
O በክልል አቀፍ ደረጃ እየለማ ያለውን የመስኖ መሬት መጠን የመረጃ ክፍተት ተዓማኒ በሆነ መልኩ በዘለቄታዊነት ያለውን የመሬት መጠንና የውሃ ማልማት አቅም ጅኦ-ሪፈረንስና ሪሞት ሴንሲንግ ተክኖሎጂ በመታገዝ መረጃን በመያዝና በመተንተን በመስኖ በይነ መረብ የመረጃ ስርዓት ውስጥ ማደራጀት፤
O የአነስተኛ ይዞታ መስኖ ልማት እንዲስፋፋ የፖሊሲና ስትራቴጂ አቅጣጫዎችን መንደፍ፣ ሲፈቀዱም ከክልሎች ጋር በቅንጅት ተግባራዊ ማድረግና አፈፃፀማቸውን መከታተል፣
O የአነስተኛ ይዞታ መስኖ ልማት አውታሮች ቅድመ ግንባታ (ጥናትና ዲዛይን)፣በግንባታ ወቅትና ድህር ግንባታ የመስኖ ተጠቃሚው ማህበረሰብ ሚና ድርሻና ሃላፊነትን በመለየት፤የመስኖ ልማት ፈንድ ምንጮችን በመለየት መተግበሪያ መመሪያና አሰራር ስርዓት መዘርጋት፤
O ከተቋሙ ራዕይና ተልዕኮ በመነሳት የሥራ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፤
O የሥራ ሂደቶች ቅንጅትና ትስስር በማጥናት የተጠናከረና ተመጋጋቢነት ያለዉ የሥራ ግንኙነት እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
O ከሥራ ዕቅዱ በመነሳት ለዳይሬክቶሬቱ የተመደበዉ በጀት በትክክል ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ይቆጣጠራል፣ ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤
O የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ የአፈር ለምነት ማሻሻያ ቴክኖሎጂዎችን እና አሰራሮችን በማመንጨትና በማላመድ እንዲሁም ተሞክረው ውጤታማ የሆኑ ምርጥ ተሞክሮዎችን በሁሉም አርሶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች እንዲተገበሩ የሚመለከታቸውን አካላት በማስተባበር ተግባራዊ ያደርጋል፤
O የአፈርን ለምነት እና ምርታማነት ለማሻሻል የሚያስችሉ የፖሊሲ እና የስትራቴጂ ሃሳቦችን ያመነጫል፣ ሲፀድቁም ተግባራዊ ያደርጋል፤
O በሁሉም ዞኖች የአፈር ለምነት ኤክስንቴሽን አገልግሎት ለማስፋፋት የዞኖቹን የመፈፀም አቅም ይገነባል፣ የማማከር አገልግሎት ይሰጣል፣ የተሟላ ክትትልና ድጋፍ በማድረግም ቴክኖሎጂዎቹ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
O የአርሶ አደሩን እንዲሁም የግል ባለሃብቱን ግንዛቤ ለማዳበር የአፈር ለምነት ማሻሻያ ቴክኖሎጂዎች ስርፀት ለማፋጠን የሚያስችሉ የአፈር ለምነት ማሻሻያ ትምህርቶችን በመገናኛ ብዙሃን፣ በበራሪ ፅሁፎች ፣በመፅሄቶች እና በፖስተሮች እና በሌሎች የመገናኛ ዘዴዎች የማስተዋወቅ እና የማስፋፋት ስራ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ይሰራል፤
O በክልል ደረጃ በአፈር ለምነት ዙሪያ የሚሰሩ አካላት ተቀናጅተው እንዲሰሩ የሚያስችል የአሰራር ስርአት ይፈጥራል፣ የማስተባበር እና የመቆጣጠር ስራዎችንም ያከናውናል፤
O የአፈር ሀብት እና ለምነት ደረጃ በማወቅ፣ በመተንተን እና በአፈር ምርመራ ውጤት ላይ በመመስረት እንዲሁም የምርምር ውጤቶችን መሰረት በማድረግ የአፈር ለምነትን የሚያበለፅጉ ቴክኖሎጂዎችን ምክረ ሃሳብ በማዘጋጀት ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
O ከአፈር ለምነት ስራ ጋር በተያያዘ ለዳይሬክቶሬቱ የሚያስፈልጉ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችንና ግብአቶችን የማሟላት እና የማደረጀት ስራ ይሰራል፤
O የአፈር ማበልጸጊያ ግብዓቶችን ማምረትና ማሰራጨት ሥራዎች ላይ የተሰማሩ አምራች ድርጅቶችን የግብዓት ጥራት ደረጃ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል እንደ አስፈላጊነቱም የመፈጸም አቅማቸውን ይገነባል፤
O ለአርሶ አደሩ የሚቀርቡ የአፈር ማበልጸጊያ ቴክኖሎጂዎች የጥራት ደረጃ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙንም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ይከታተላል፤
O በተለያዩ አካላት ለሚገቡ አዳዲስ የአፈር ለምነት ማሻሻያ ቴክኖሎጂዎች ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ይሠራል፡፡
O. ዘርፉ ከስሩ የሚከተሉት ዳይሬክቶሬቶችን ያስተባብራል፡-
o. የአነስተኛ ይዞታ መስኖ ልማት ዳይሬክቶሬት
o. የተፈጥሮ ሀብት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት
o. የአፈር ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU