CERS-Bureau of Agriculture
የግብርና እድገት ፕሮግራም 2 (AGP II)
የግብርና እድገት ፕሮግራም በሀገሪቱና በክልሉ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ግቦችን ለማሳካት በሚደረገዉ ጥረት ዉስጥ በሚከናወኑ ቁልፍ የትኩረት መስኮች የተቀረፁ ተግባራትን በብቃት ለመፈፀም ተቀርጾ እየሰራ የሚገኝ የልማት ፕሮግራም ነዉ፡፡
ፕሮግራሙ በመጀመሪያዉ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራን ለማሳካት በተመረጡ የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች ሲሰራ የቆየና በሁለተኛዉ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን በምእራፍ ሁለት የቀጠለ ሲሆን የግብርና አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን በመደግፍና በማጠናከር፣ የግብርና ምርምር ስራዎችን በመደገፍ እና በማጠናከር፣ የአነስተኛ መስኖ ልማት ተቋማትን በማልማትና በማጠናከር፣ በግብርና ምርቶች እሴት ሰንሰለት ስራዎችን በማከናወን እንዲሁም የፕሮግራም አስተዳደር ክትትልና ግምገማ ስራ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማከናወን በሚሉት አምስት አምዶች ተግባራቱን እያከናወነ የሚገኝ ፕሮግራም ነዉ፡፡
የተሳትፎኣዊ አነስተኛ መስኖ ልማት ፕሮግራም (PSSIDP/IFAD)
ተሳትፎኣዊ አነስተኛ መስኖ ልማት ፕሮግራም በመስኖ ልማት በመታገዝ መሠረታዊ የኑሮ መሻሻል እና የሕይወት ለዉጥ ለማምጣት የሚችሉ አነስተኛ አርሶ አደሮችን በመስኖ ልማትና ተቋማት አስተዳደር በመደገፍና በማጠናከር እንዲሁም የገበያ ትስስር በመፍጠር ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ የሚገኝ የልማት ፕሮግራም ነዉ፡፡
የፕሮግራሙ ዓላማ በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማሻሻል፣ ድህነትን በዘላቂነት ለመቅረፍ፣ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የምግብና ስርዓተ-ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲሁም የዓየር ንብርት ለዉጥን የሚቋቋም የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ይሰራል፡፡
ፕሮግራሙ የአነስተኛ መስኖ ተቋማት ልማትና አዉታር ዝርጋታ፣ በዘላቂ ግብርና አቅም ግንባታ ኢንቨስትመንት፣ በፕሮግራም ማኔጅመንት፣ በድጋፍና ክትትል እንዲሁም በእዉቀት አስተዳደር (Knowledge Management) በሚሉት ሶስት አምዶች የተከፋፈሉ ስምንት የልማት አጀንዳዎችን በመቅረጽ በተመረጡ የክልሉ የፕሮግራም አካባቢዎች ተግባሩን እያከናወነ ይገኛል፡፡
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU