• Call Us
  • +25146 554 16 87

የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም

                             የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለግብርና ቢሮ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት አለው፡-

O የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ የፖሊሲ ሃሳቦች፣ የህግ ማዕቀፎች፣ የሥራ መመሪያዎች፣ ማንዋሎች፣   የአሠራር ሥርዓቶች፣ በጥናት ተደግፈው እንዲወጡና እንዲሻሻሉ ይሠራል፣ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፣ ውጤታማነታቸውን ይከታተላል፤

O የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስራዎችን ውጤታማ የሚያደርጉ ስትራቴጂዎችን ተግባር ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤

O የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አሰራር በተመለከተ ምርጥ ተሞክሮዎችን እንዲቀሙሩና እንዲስፋፉ ያደርጋል።

O የመሬት መጠቀም መብት ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችሉ ጥናቶች እንዲካሄዱ ያደርጋል፤ የጥናት ውጤቱም ወደ ተግባር የሚለወጥበትን መንገድ ያመቻቻል፡፡

O የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አሰራርን እና የመሬት አጠቃቀም ፖሊሲና ፕላን ዝግጅቱንና አተገባበሩን የሚያግዝ ለባለሙያዎች፣ ባለድርሻ አካላትና ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንዲከናወኑ ያደርጋል፤ የማስፈፀሚያ አቅምን በማደራጀት ተገቢ የማብቃት ሥራ እንዲከናወን ያደርጋል፤

O በክልል አቀፍ ደረጃ እያንዳንዱ ማሳ መሬት ለምን ዓላማ መዋል እንዳለበት እንዲጠና በማድረግ ቴክኒካል ሪፖርት ያቀርባል፤

O የክልሉን የእርሻ፣ የደን፣ የግጦሽ፣ የዉሃ አካላት፣ መሠረተ ልማቶች እና ለሌሎች የግንባታ ቦታ ሥርጭትና ጠቀሜታ እንዲጠና በማድረግ፤ ለመሬት አጠቃቀም  ፕላን ዝግጅት ግብዓት እንዲሆኑ ያደርጋል፤

O የክልሉ የመሬት እምቅ ሀብት ደረጃ እንዲጠና በማድረግ የመሬት እንስሳትን የመሸከም አቅም ትንበያ ሥራ እንዲከናወን ያደርጋል፤

O ከዞን እስከ ቀበሌ የመሬት አጠቃቀም ሥርዓት ግንባታ እንዲዘረጋ እና የመሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅት፣ ትግበራና ቁጥጥር ሥራዎችን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤ከዞኖች ጋር ይሠራል፣ ሙያዊ እገዛ እንዲያገኙ ያደርጋል፤

O በተለያዩ የመሬት አጠቃቀም መካከል ግጭትና ሽሚያ ሲፈጠር በጥናት የተደገፈ የውሳኔ ሃሳብ በማዘጋጀት ለውሳኔ ሰጭ አካላት ያቀርባል፤

O በክልሉ ጎጂ የመሬት አጠቃቀም ላይ የቁጥጥር ተግባር ስለሚከናወንበት ሁኔታ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ስትራቴጂ ይቀይሳል፣ ቁጥጥር እንዲደረግም ያደርጋል፤

O ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላትና የተለያዩ ተቋማትን በመቀናጀት የአገሪቱን ስነ-ምህዳር ቀጠናዎች ክፍፍል እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤

O ለየአካባቢው ተስማሚ የሆኑ አዳዲስ የጥናትና የምርምር ውጤቶችን ያካተተ የመሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅት ፓኬጆችን እንዲዘጋጁና እንዲተገበሩ ያደርጋል፤ ወቅታዊ የመሬት አጠቃቀምና ሽፋን ካርታና ሰነድ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤

O የገጠር መሬት ይዞታ መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት አመዘጋገብ ህግና ሥርዓቱን ተከትሎ እየተካሄደ ስለመሆኑ በክትትልና ድጋፍ እንዲረጋገጥ ያደርጋል/ ያረጋግጣል፤

O የካዳስተር መረጃ አሰባሰብ፣ አደረጃጀት ስርጭት እና የካዳስተር ካርታ አዘገጃጀት በስታንዳርዱ መሠረት መፈፀሙን ድጋፍና ክትትል እንዲረጋገጥ ያደርጋል /ያረጋግጣል፡፡

O ለካዳስተር ካርታ ግብዓት የሚሆን የኦርቶፎቶና የመስመራዊ ካርታ ዝግጅት ሂደትን ያስተባብራል ይመራል፤አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤ ያረጋግጣል

O ከመስክና ከተለያዩ ምንጮች የሚሰበሰቡ መረጃዎችን የጂ.አይ.ኤስ ሶፍትዌር በመጠቀም ለህጋዊ ካደስተር ስርዓት ጥቅም ላይ የሚውሉበትን አግባብ ክለላዊ ስታንዳርድ መሠረት ስለመሆናቸው ይከታተላል፤

O የአየር ፎቶግራፍ/የሳተላይት ምሥሎችን እስታንዳርድ ያዘጋጃል፣ እንዲሁም የማስነሳትና ግዥ አፈፃፀሙን ሥራ ይመራል ያስተባብራል፤

O ለመሬት አጠቃቀም ፕላን ግብዓት የሚሆኑ ክልላዊ ደረጃ የተሰበሰቡ የጂኦ ስፓሻል መረጃዎች በየጊዜው ክትትልና ግምገማ በማድረግ ተገቢውን መረጃ መያዛቸውንና ደረጃቸውን (standard) ያረጋግጣል፣የመረጃ ሥርዓት ማደራጀትና ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ ያደርጋል፤

O የመሬት ሀብት፣ የመሬት አጠቃቀም ፕላኖችን፣ የስነ-ምህዳር እና የመሬት አጠቃቀምና ሽፋን መረጃዎችን በዳታ ቤዝ እንዲደራጁ ያደርጋል፣ ለተጠቃሚዉ በወቅቱ እንዲሰራጩ ያደርጋል፤

O የመሬት ይዞታ መረጃዎችና እና ሌሎች የምዝገባ ቅጂዎችን ህጋዊ ለሆነ አካል የሚሰጥበትን ስርዓት ይዘረጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል

O ለመብት ክልከላና ኃላፊነቶች የተዘጋጁት ክልላዊ የገጠር መሬት አስተዳደር መረጃ ስርዓት በአግባቡ የተከናወነባቸው ስለመሆኑ ይከታተላል፣ ችግር ሲያጋጥም መፍትሄ ይሰጣል፤

O የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ዳታ ቤዞች እንዲመሠረቱ ያደርጋል፣ አጠቃቀማቸውን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ የመረጃዎች ቅጂ /backup/ ፋይል በአግባቡና በሚፈለገው ደረጃ መያዛቸውና መጠበቃቸውን ይከታተላል፣

O ለሴክተሩ ባለሙያዎች፣ በየግብርና ለተሰማሩ ባለሀብቶችና ቡድኖች የአቅም ግንባታ ሥልጠና፣ ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ትምህርትና ሥልጠና ስትራቴጂ ይቀይሳል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣ውጤቱንም ይገመግማል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል::