CERS-Bureau of Agriculture
የቡና፤ ቅመማ ቅመም ልማትና ግብይት ባለስልጣን ተጠሪነቱ ለግብርና ቢሮ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት አለው፡-
O በቡናና ቅመማ ቅመም ልማት የተሳለጠ የኤክስቴንሽን አገልግሎት በመስጠትና ግልጽ፤ ቀልጣፋና ዘመናዊ የግብይት ስርዓት በመዘርጋት፤ ምርትን በጥራትና በብዛት ተዘጋጅቶ ለሃገር ውስጥና ለወጪ ገበያ እንዲቀርብ በማስቻል አምራቹና የግብይት ተዋኒያኑ የተሻለ ገቢ አግኝተው ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ማሳደግ ሲሆን ባለሥልጣኑ የሚሠጠው አገልግሎት (ዋና ዋና ተግባራት)፡-
O በክልሉ ዘመናዊ የቡናና ቅመማ ቅመም ሰብሎች ልማትና ግብይትን ለማስፋፋት፣ ለማጠናከርና መልካም ተሞክሮዎችን ለመቀመር የሚረዱ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ያዘጋጃል፣ ያሻሽላል፣ ሕጎችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን ባለድርሻ አካላትንና ተገልጋዮችን በማሳተፍ ያዘጋጃል፣ ለመንግስት አቅርቦ ያጸድቃል፣ ተግባራዊም ያደርጋል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
O አነስተኛ ይዞታ ባለው አርሶ አደር እና በአልሚ ባለሀብት የሚለማ ቡናና ቅመማ ቅመም በቴክኖሎጂ፣ በተሻሻለና ዘመናዊ አሰራር ተሳትፏዊ የኤክስቴንሽን ድጋፍን በማጠናከር ምርታማነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ይሰራል፤
O በቡናና ቅመማ ቅመም ልማት ሂደት አርሶ አደሩና ባለሀብቱ በግል ማሳቸዉና በወል መሬት ላይ ውጤታማ የሆኑ የአፈር ለምነት ማሻሻያ በአግባቡ በማከናወን የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራዎች መካሄዳቸዉን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣
O ለቡናና ቅመማ ቅመም ልማት ነባርና አዳዲስ አካባቢዎች የተስማሚነት ደረጃ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በጥናት ይለያል፣ እንደየ ሥነ-ምህዳሩ ምርት፣ ምርታማነትንና ጥራትን ለማሳደግ የሚያስችል ዘመናዊ የአመራረት ዘዴ ለማስፋት ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣
O ለቡናና ቅመማ ቅመም ልማትና ግብይት አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች ስፔሲፊኬሽን ያዘጋጃል፣ ለተጠቃሚዎች በወቅቱ እንዲቀርብ ይደረጋል፣አጠቃቀሙንም ይከታተላል፤
O የቡናና ቅመማ ቅመም ሰብል በሽታዎች፣ ተባይና አረም ክስተቶችን አሰሳ ያካሄዳል፣ ይለያል በምርት ላይ የሚያደርሱትን ተጽዕኖ ለመቀነስ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የመከላከልና የመቆጣጠር እርምጃ ይወስዳል፣
O ከዞኖች/ከልዩ ወረዳዎች/ከከተማ አስተዳደር፣ ከምርምርና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና አግባብነት ካላቸዉ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር አርሶ አደሮች፣ አልሚ ባለሀብቶች እና የንግዱ ማህበረሰብ በቡናና ቅመማ ቅመም ልማትና ጥበቃ፣ ጥራት ቁጥጥርና ግብይት አቅማቸውን በቀጣይነት ለማሳደግ የሚያስችል አገልግሎት በመስጠት የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎች እና መልካም ተሞክሮዎች እንዲስፋፋ ድጋፍ ይሰጣል፣ ውጤታማነታቸውንም ይከታተላል፤
O የቡናና የቅመማ ቅመም ምርት ማሳደጊያ እና ማዘጋጃ ግብዓቶችን፣ ማሽነሪዎችን፣ የምርት ማሸጊያዎችንና የጥራት መቆጣጣሪያ መሣሪያዎች ለአምራቾች፣ ምርት አቅራቢዎች፣ ለአዘጋጆችና ለቡና ቆይዎች በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡበት አሠራር የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍ ይዘረጋል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፣
O ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመቀናጀት ዘመናዊ የቡናና ቅመማ ቅመም ልማትና ግብይት ለማስፋፋትና ዘርፉን ለማጠናከር፣ በእሴት ሰንሰለቱ የሚታዩ ማነቆዎችን ለመለየትና ለመፍታት የሚያስችሉ ጥናቶችን ያካሂዳል፤ የመፍትሔ አቅጣጫም ያስቀምጣል፡፡
O በቡናና ቅመማ ቅመም ምርት ላይ እሴት መጨመር፣ ንግድ ወይም ዝግጅት ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ ባለሃብቶችንና ነጋዴዎች የብቃት ማረጋገጫ ይሰጣል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፤ ዝርዝራቸዉንም ለንግድ ቢሮ ያስተላልፋል፤
O ወደ ውጭ የሚላኩ የቡና እንዲሁም እንዳስፈላጊነቱ የቅመማ ቅመም ምርቶችን የጥራትና ጣዕም ምርመራ በማድረግ ደረጃ በመስጠት ወደ ፌደራል ሽኝት ማዕከል አሽጎ ይልካል፤
O የቡናና የቅመማ ቅመም ምርቶችን ዘመናዊ ግብይት ሥርዓት ይዘረጋል፣ አፈጻጸሙን ይደግፋል፣ ይከታተላል፤ የምርቶቹን ሕገ-ወጥ ግብይትና ዝውውርን አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ይከላከላል፣ይቆጣጠራል፣
O ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመተባበር የቡናና ቅመማ ቅመም ወጪ ንግድ በነባርና አዳዲስ ገበያዎች የሚያድግበትን አሠራር ሥርዓት ዘርግቶ ውጤታማ የገበያ ማስፋፊያ ሥራ ይተገብራል፣የቡናና ቅመማ ቅመም ምርት ክምችት ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
O በቡናና ቅመማ ቅመም ልማትና ግብይት ወቅታዊ፣ ክልላዊ፣ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ የምርትና ግብይት መረጃዎችን፣ ይሰበስባል፣ ያደራጃል፣ ይተነትናል፣ ትንበያዎችን ያካሄዳል፣ በየወቅቱም ለተጠቃሚዎች ያሰራጫል፤
O የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ ፍላጎቶችን እና ችግሮችን ይለያል፤ ቅደም ተከተል ያወጣል፣ ችግሮቹ የሚፈቱበትን አሠራር ይዘረጋል፤አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡
O በቡናና ቅመማ ቅመም የወጪ ንግድ ተጠቃሚነታችንን ለማሳደግ በምርቶቹ ላይ እሴት ለመጨመር የሚያስችል ሀገራዊ አቅም እንዲገነባ ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት ይሠራል፣ በምርቶቹም ወደ ዓለም ገበያ ለመግባት የሚያስችል ስልት ይነድፋል፣ ተግባራዊም ያደርጋል፤
O የስልጠና ሞጁሎችን በማዘጋጀት በአርሶ አደር ማሠልጠኛ ማዕከል ስልጠና ይሠጣል፣
O በቡናና ቅመማ ቅመም ልማት፤ጥበቃ፤ ግብይት፤ጥራት አጠባበቅና አቅርቦት ላይ ውጤታማ የሆኑ አርሶ አደርችን፣ አልሚ ባለሃብቶችንና ማህበራትን በመለየት የማበረታቻ ሽልማትና ዕዉቅና የሚሰጥበትን አሰራር ያዘጋጃል፣ ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
O በቡናና ቅመማ ቅመም ኢንቨስትመንት/ልማት ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች የአካባቢውን የተፈጥሮ ሀብት እንዲጠብቁና ለአርሶ አደሩ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረጋቸውን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ይከታተላል፤
O የቡናና ቅመማ ቅመም ልማት ከአየር ንብረት ለዉጥ መቋቋሚያ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ጋር በተጣጣመ መልኩ የሚከናወንበት ሥርዓትና አሰራር ይዘረጋል፣ ተግባራዊነቱን ይከታታላል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣
O የቡና ላኪዎች፣ ማዘጋጃና ማከማቻ ኢንዱስትሪዎች፣ ቡና ቆይዎች፣ ህብረት ሥራ ማህበራት ዩንዬኖች በተሰጣቸው የብቃት ማረጋገጫ መሰረት መሥራታቸውን ክትትልና ቁጥጥር ያድርጋል፣
O ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ግብዓቶችን በሚፈለገው ዓይነት፣ መጠን፣ ጥራት፣ ቦታና ወቅት ለማቅረብ የሚያስችል ውጤታማ የሆነ የአሰራርና የመረጃ ሥርዓት በመዘርጋት፣ ብቃትንና ጥራትን በማረጋገጥ ተግባራዊ ያደርጋል፣
O ለየስነ-ምህዳሩ ተስማሚ የሆኑ ከምርምር የሚወጡ አዳዲስ የቡናና ቅመማ ቅመም ቴክኖሎጂዎችን አቅርቦት ለመፍጠር ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመቀናጀት የተስማሚነት ቅድመ-ሙከራ ያካሂዳል ፤ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU