CERS-Bureau of Agriculture
የ20-20-10 የእንሰት ተክል ፕሮጀክት (50 የእንሰት ተክል ለአንድ ቤተሰብ) ፕሮጀክት፡
የእንሰት ችግኝ ብዜትና ስርጭት፣ የእንሰት በሽታ መከላከል፣ የእንሰት ድህረ-ምርት ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና ምርታማነትን ማሻሻልን ያካተተ የምረትና ምርታማነት ማሳደጊያ ስልት ነው፡፡ ይህ ኢኒሼቲቭ እንሰትን በክልላችንና በሀገራችን ከመጥፋት ወደ ማስፋፋት ለመቀየር እና ከእንሰት የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎችን ክልላችንና ሀገራችን ማግኘት እንድትችል የሚረዳ ነው። በመሆኑም እንሰት የሚሰጠውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ኢኮሎጂያዊ ጥቅሞችን ለማግኘት አንድ ቤተሰብ ከ50 -100 እንስት እንዲኖረው እየተሰራ ነው። የአፈፃፀም ስልቱም በሀምሳው ላይ ለመጀመር 20-20-10 በሚል የአፈፃፀም ስልት ተጀምሮ እያደገ እንዲሄድ ታቅዶ እየተተገበረ ያለ ኢኒሺዬቲቭ ነው። ይህ ማለት በመጀመሪያው አመት በትንሹ 20 የእንሰት ችግኝ፣ በሁተኛው አመት 20 እና በሶስተኛው አመት 10 የእንሰት ችግኝ እያንዳንዱ የክልሉ አርሶ አደር እንዲተክል በማድረግ አቅም ያለው አርሶ አደር ግን በአንድ አመት ከ100 በላይም መትከል እንዲችል እየተደገፈ ነው። የእንሰት ፕሮጀክቱ ቅድሚያ ትኩረት አድርጎ የሚጀምረው ዝናብ አጠር በሆኑና ድርቅ በሚያጠቃቸው እና የምግብ ዋስትና ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ ይሆናል። ከዚህ ቀጥሎ ወደ ደጋማው በማስፋፋት ይሰራል። የእንሰት ፕሮጀክቱ ትኩረት ተደርጎ የሚሰራው ልማቱን በማስፋፋት፣ ድህረ ምርቱ ቴክኖሎጂ ላይ በተለይም እንሰትን በዱቄት መልክ ወደ ገበያ ማስጋባት ብቻ ሳይሆን የቆጮ ዱቄት ኤክስፖርት ማድረግ ላይ በልዩ ትኩረት ይሰራል። በዚህ መሰረት በ2015/6 ብቻ የእንሰት ማሳ ሽፋን ለማሳደግ በቁጥር 84,239,080 ችግኝ በ33,693 ሄ/ር በ478,676 (ወንድ 417,149፣ ሴት 61,527) አ/አደሮች ማሳ ተከላ ለማካሄድ የአ/አደር መነቃቃት ከመፍጠር አንፃር የዚህ ኢኒሺዬቲቭ ሚና የጎላ የነበረ ሲሆን በተመሳሳይ በሁሉም ክልሉ አካባቢዎች ለ2016/7 ተከለ የሚሆን አምቾ በአርሶ አደር ከሚለማው 1,552,003 አሚቾ በተጨማሪ በተቋማት ጭምር እንዲሰፋ በማድረግ 255,864 አሚቾ በድምሩ 1,807,863 አምቾ ቀበራ እንዲካሄድ በማድረግ 90,487,044 ችግኝ እንዲዘጋጅ ከማድረግ አንፃር የዚህ ኢኒሺዬቲቭ ድርሻ ጉልህ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU