CERS-Bureau of Agriculture
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ሎጎ ቀለማትና ትርጓሜያቸው
የቢሮውን አዲስ አደረጃጀትና አወቃቀር ተከትሎ የተረቀፀውን ራዕይና ተልዕኮ የሚወክል ሎጎ አዘጋጅቶ ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ፣
ሎጎው ከተለያዩ ቀለማት - ቅርፅ እናመስመሮች በመጠቀም የግብርና ቢሮ ዓላማ በሚያሳይ መልኩ መለያ ምልክት በማረግ አዘጋጅቶ ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ፣
አርማው - ዕምቅ የተፈጥሮ ሀብትና የመልማት አቅምን ይቀክላል፡፡ ይህም ማለት የፀሐይ ብርሃንን፣ ለም መሬትን እና የውሀ ሀብትን ያመለክታል፡፡ ይህም በተራው የግብርና ልማት ዕድገትን፣ ጤናማ ህይወትን፣ የኃይል ምንጭነትንና ልባዊ የመበልጸግ ስሜትን ያመለክታል፡፡
ቢጫው ቀለም
የፀሐይ ብርሃንን ይወክላል፡፡ ሀገራችንም ሆነች ክልላችን የ13 ወራት ፀሐይ የፀጋ ባለቤት መሆናችንን፣ ለኑሮ ተስማሚነትና ለቢዝነስና ኢንቬስትመንት ያለንን አመቺነት እንዲሁም የመልማት አቅም ባለቤት መሆናችንን ያመለክታል፡፡
አረንጓዴው ቀለም
የሀገራችንንና የክልላችንን ልምላሜና የአፅዋት ሽፋል ያመለክታል፡፡ ክልችን ያለውን የልማት ዕድገት ሰፊ ዕድል፣ ብግብርናችን የሚመረተውን ምርት ተፈጥሯዊነት እና ትኩስነት እንዲሁም የግብርና ልማታችንን ውጤታማነት ያመለክታል፡፡ ክልላችንም ለግብርና ቢዝነስና ኢንቬስትመንት አመቺነት ያለው ሰፊ የመሬት ሀብት ባለቤት መሆናችንን ያሳያል፡፡
ሰማያዊው ቀለም
የውሃ ሀብታችንን፣ የተረጋጋ የግብርና ክፍለ ኢኮኖሚን፣ አስተማማኝና ታማኝነት ያለው የዕድገት ዕድል የታደልን መሆኑን የሚመለክት ሲሆን የክልላችን አርሶና አርብቶ አደሮች ለኢንዱስትሪ ልማት የጥሬ ዕቃና ግብዓት በማቅረብ የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡበትን ሁኔታ ይወክላል፡፡
ቡናማው ቀለም
የመሬት ሀብትን በተለይም ለም አፈርን፣ ግብረ-ገብነትን፣ ታማኝነትን እንዲሁምየግብርና ልማታችንን ለማዘመንና ለማሳደግ ያለንን ፅኑ ፍላጎትና ተነሳሽነት በሙሉ የሚያጠቃልል ውክልና ያለው ነው፡፡
በተጠቀሱት ቀለማት የተቀመጡት መስመሮች
ግልፅ ቅርፆች የሸክላ ሠሪ ዕደ ጥበብYxene፣ ቅርጫት፣ በሸማ ላይ የሚገኝ የልብስ ዲዛይን እና የእንሻ መሣሪያ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ትይዩ መስመሮቹም በአልባሳት ብቻ ሳይሆን በውኃ አካላትም ላይ ሊከሰቱና ሊታዩ የሚችሉ መሆኑን ያመለክታል፡፡
የሎጎው ክብ ቅርፅ
የሎጎው ክብ ቅርፅ የሚያመለክተው ሁሉም የግብርና ልማት የትኩረት መስክ፣ የተፈጥሮ ሀብት፣ የግብና ቴክኖሎጂዎችና የአሠራር ዘይቤዎች፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና የንግድ ዘርፍ በአጠቃላይ በዚህ ክብ ቅርጽ ሥነ-ምኅዳር ውስጥ እንደሚታቀፍ የሚያመለክት ነው፡፡
እንሰቱ
የክልሉ ህዝቦች የጋራ መገለጫ፣ የብዝሃነትና የተስፋ ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሰደው የእንሰት ሰብል በሎጎው መካከል ላይ መቀመጡ የሚያመለክተው የክልሉን ህዝቦች ፍትህ አዋቂነትን ነው፡፡ እንሰት ከክልሉ ሁሉም ስነ-ምኅዳራት ጋር የሚስማማና በሁሉም አካባቢዎች የሚለማ፣ ውኃን በውስጡ የማቆየት አቅሙ ድርቅን ተቋቁሞ ከፍተኛ ምርት ከመስጠት በተጨማሪ ከከባቢያዎ ሁኔታዎች ጋር የተጣጣመ መስተጋብር ያለው፣ በንጥረ-ምግብ ይዘቶች የበለፀገ፣ ለምግብና ሥርዓተ-ምግብ ዋስትና መረጋገጥ ጉልህ ሚና የሚጫወት እንዲሁም ለሌሎች ማኅበረ-ባህላዊ ዕሴቶች መጎልበት አስተዋፅዖ ከማበርከት በተጨማሪ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚያስገኝ ሰብል መሆኑን ያመለክታል፡፡
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU