• Call Us
  • +25146 554 16 87

30-40-30 ፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት

                                              30-40-30 ፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት

30-40-30 የፍራፍሬ ፕሮጀክት ኣላማ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት የበለጠ ለማስፋት ከመደበኛ የፍራፍሬ ተከላ በተጨማሪ የወረዳዎች/የቀበሌዎች የፍራፍሬ ፖቴንሻል መሰረት ልዩ ድጋፍ በማድረግ በአንድ / ጓሮ በመጀመሪያ አመት 30 በሁለተኛ አመት 40 በሶስተኛ አመት 30 በመትከል በአጠቃላይ 3 ዓመት ውስጥ አንድ /አደር ቢያንስ 100 ፍራፍሬ ችግኝ እንዲተክል ድጋፍ የሚሰጥ ሲሆን በዚህ ፕሮጀክት የተመረጠ መንደር ቢያንስ 100 /አደሮች ተሳታፊ በማድረግ የሚተገበር ነው፡፡ በተመሳሳይ በእምነት ተቋማት እና በመንግስት ተቋማት 100 - 10,000 የፍራፍሬ ችግኞች 3 አመት መትከልን ታሳቢ ያደረገ ሲሆን የተመረጡ ፍራፍሬ አይነቶችም መዝ፣ ፓፓያ፣ አቮካዶ እና አፕል ናቸው፡፡ ተግባሩ በሁለት አመት ውስጥ ውጤት የተመዘገበበት ኢንሺዬቲቭ ነው፡፡ በዚህ መሰረት 2015/6 በመኸር ወቅት 30-40-30 ፕሮጀክት በቁጥር 643,195 የፍራፍሬ ችግኝ 1,056 / ማሳ ተከላ በማከናወን አስደናቂ ውጤት የተመዘገበበት ነው፡፡