CERS-Bureau of Agriculture
አዳድስና ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ጥራት ያለዉን ምርት እንዲያመርት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ
ህዳር 13/2016 ዓ/ም
አዳድስ ዘመናዊ የግብርና ቴክኖልጂ ምርትና ምርታማነትን ከመጨመሩም ባሻገር አርሶ አደራችን ከብዙ እንግልትና ልፋት በመላቀቅ ጥራት ያለዉን ምርት ጭምር እንዲያመርት ከፍተኛ ሚና እንዳለሁ የተገለፀ ሲሆን
የክልሉ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ተቋም (ATI) ከአዳድስና ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎች ዉስጥ አንዱ የሆነዉን የበቆሎ መፈልፈያ ማሽን(Maize thresher) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል#በሀላባ_ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ በጎፌሳ ቀበሌ የቦቆሎ ዉቅያ እየተከናወነ ይገኛል።
የአከባቢው አርሶ አደሮችም በቴክኖሎጂዉ(በመፈልፈያ ማሽኑ) ምርታቸውን በፍጥነት በማንሳት ከዝናብ እና ከሌሎችም ምርትን ከሚጎዱ ድርጊቶች ምርታቸውን ከመታደጋቸዉም በተጨመሪ ከበህላዊና ከተለመደው የምርት መዉቂያ እንግልትና ልፋት እራሳቸውን ነፃ እያደረጉም መሆናቸውን ግብርና ጽ/ቤት ገልጾዋል። #አቶቲ_ኡሎ_ወረዳ_ግብርና_ጽ/ቤት
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU