CERS-Bureau of Agriculture
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ግብርና ቢሮ የ2017 የግማሽ ዓመት የዋና ዋና ግቦች አፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር የአስተሳሰብና የግንዛቤ ለውጥ በማጎልበት ድህነትን በቤተሰብ ደረጃ በማሸነፍ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
ለዚህም ግብርናን በማዘመን በትጋት ድህነትን ለማሸነፍ የግብርና ባለሙያዎች ሚናቸው ከፍተኛ እንደሆነ አብራርተዋል።
በዚሁም መሰረት ባለፉት ስድስት ወራት በግብርናው ዘርፍ ከዕቅድ ዝግጅት ጀምሮ የተቋሙን የማስፈጸም አቅም ግንባታ ለማሳደግ በቅንጅት በመሰራቱ በሁሉም ዘርፎች ለውጥ እየመጣ መሆኑን አስረድተዋል።
በተለይ ደግሞ ስድስቱን የግብርና ምሰሶዎች ለማሳካት በትኩረት በመሰራቱ ተጨባጭ ለውጥ እየመጣ ይገኛል ብለዋል።
ይህም ለቀጣይ ስራ የሚያነሳሳና ብርታት የሚሰጥ መሆኑን የገለፁት አቶ ኡስማን የታቀዱ ግቦች እንዲሳኩ ስራዎችን በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በዛሬው ውሎ በመድረኩ ላይ የክልሉ ግብርና ቢሮና የተጠሪ ተቋማት የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በነገው ዕለት ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል።
በመድረኩ ላይ የክልሉ ግብርና ሴክተር የስራ ሀላፊዎች፣ የፕሮጀክትና ፕሮግራም አስተባባሪዎች እንዲሁም የሴክተሩ
ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU