CERS-Bureau of Agriculture
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ዶ/ር የዘንድሮውን የ2017 የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል።
የዘንድሮውን የተቀናጀ የበጋ የተፋሰስ ልማት ክልላዊ ንቅናቄ በይፋ ከጀመርን ወዲህ ፣ተግባሩን ለማሳካት በየአካባቢው እየታዪ ያሉት የህብረተሰብ ተሳትፎዎች አበረታች መሆኑን ገልፀዋል።
የተቀናጀ ተተፋሰስ ልማት ንቅናቄዉ ግለቱን ጠብቆ እንዲቀጥል ማድረግ እንደሚያስፈልግ የገለፁት ርዕስ መስተዳድሩ የሥነ አካላዊ ሥራዎችም ጥራታቸዉን የጠበቁና የአፈርና የዉኃ አካላትን ጤንነት በመጠበቅ ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻልና የአየር ንብረት ለዉጥን ለመከላከል የሚያግዙ እንዲሆኑ በትኩረት መሥራት ይጠበቃል ።
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU